Pinned Tweet
"ሀገር የምትራመደው በአንድ ሳንቲ ሜትር ዕውቀት፣ በመቶ ሳንቲ ሜትር ስነ-ስርዓት ነው"
#ሕማማትና_በገና
አዲስ መተግበሪያ/ Application 🚀
አዳም ረታ የፈጠራቸውን አዳዲስ ቃላት ትርጉም የያዘ "ሙዛፈር" የመዝገበ ቃላት መተግበሪያ (application) Download 👇
Adamretabooks.et/muzafer
በድሮ ጊዜ ቀስት ሲሰራ ቂጡ ላይ ለሚዛን ላባ ይገባለታል። እና አንድ ጭልፊት ጎኑን በቀስት ተመትቶ ከሰማይ እየወደቀ፣ ዞር ብሎ የተወጋበትን ቀስት ሲያይ የራሱ አይነት ላባ ተሰክቶበት አየ...
በወገንህ እጅ እንደመጥፋት ከባድና ቀላል ነገር የለም
#የቀ
"ሚሪንዳ ሆንኩ።
(እከሌ 'ሚሪንዳ' ነው ማለት፤ 'ሴታ ሴት' ነው ማለት ነው በእኔ አማርኛ"
#የስንብት_ቀለማት
"መስዋዕትነት ምንድን ነው?
ለእኔ፤ 'መስዋዕትነት'፤ ቀን በቀን ከላያችን ላይ የሚሸራረፈው የትዕግስት ሀብታችን ነው።
ከላያችን እየበነነ የሚሄደው የልጅነት ሰፈፍ ነው።
የኖረ ሁሉ፤ በሆነ መልክ መስዋዕት ነው።"
***
#የስንብት_ቀለማት
"...ፈረንጆች 'እንትና ኤልዛቤት ቴይለርን ትመስላለች'፣ ወይም 'ቬኑስን ትመስላለች' ይላሉ። የእኛ ሴቶችስ? ከጊዜ፣ ከታሪክ ጋር የተገናኙ ታላቅ እንስቶች ኪነታችን አልወለደም። ኪነታችን አልፈጠራቸውም። እንተኛቸዋለን እንጂ አላወቅናቸውም"
#እሎሽ
'ጎበዝ ሀገር የተወለድኩ ነኝ' ለማለት ምን ላሳያቸው?
የአድዋ ጦርነት?
ሉዓላዊነት ማሺንና ገንዘብ አይደለም።
በገንዘብ አይሰላም።
ነፃነት ስንት አውሮፕላን ያወጣል?
#መረቅ
"ከሽንት ቤቱ መግቢያ፤ የሆነች በረሃ የመሰለች ደባሪ ገርዳሜ ሶፍት ፔፐር ታድላለች። ማነው የመጥረጊያውን መጠን የሚወስነው? የቂጣችን ስፋት ተለክቶ፤ አማሃይ ሳንቲሜትር ወጥቶለታል?
'አይበቃኝም' ብል፤ 'አራም!' ልባል ነው?! "
#የስንብት_ቀለማት
'አለማየሁ' የተባለ፤ አለማየሁ ስለተባለ አማራ ጨቆነኝ ይልና 'አሌክስ' ሲባል ግን ፈረንጅ ጨቆነኝ የማይለው ለምንድን ነው?
#የስንብት_ቀለማት
"[በዩኒቨርሲቲ] 4 ፖይንት ስታመጣ ከሚቀናብህ፣ 2 ፖይንት ስታመጣ ከሚስቅብህ ምን ትጠብቃለህ?
ይሄ አገር አማሃይ ያመልካል።"
#አፍ
"ማንም የአእምሮ ባርያ፤ የቀጥታና የእጅ አዙር ቅኝ ገዢዎች 'ጥሩ ነው' ካላሉት ጥሩ አይደለም። 'ያምራል' ካላሉት አያምርም። 'ብሩህ ነህ' ካላሉት ብሩህ አይደለም።"
#የስንብት_ቀለማት
"ጉርሻ አለማዊ ስጋ ወደሙ ነው። በግለሰቦች መሀል ያለ ቁርባን ነው። ቃል ኪዳን ነው (በእጄ በልተህ እንዲህ አታድርገኝ ... )"
#እቴሜቴሎሚሽታ
'አይ አም ኢንተለጀንት' ብሎ የሚናገር፤ ግን ዘር ማንዘሩ በቁንጫ የሚበላበት፣ በጎጥ ብራንድ የነደደ ሰው አያበሽቅህም? በ 'ነኝ' ሰው የሚበላለጥ ቢሆን የአለም ጌታዋ ብዙ ነበር።
#የስንብት_ቀለማት
"በክርስቶስ አምናለሁ የሚል ጎሰኛ ቢያጋጥመኝ፤ የክርስቶስ ሰው እንዳልሆነ አውቃለሁ፡፡ ረቂቅ ምርመራም አያስፈልግም፣ ቀኖና መመርመር ግድ አይደለም፡፡ ሺህ ጊዜ እንጥልህ በመዝሙርና በቅዳሴ ቢነድ ጎሰኛ ነህ ክርስቲያን አይደለህም
#የስንብትቀለማት
"እኔ የፊት በር ስዘጋ፤ የጀርባ በር ከፍተው፣ ጠላታቸውን አገራቸው እልፍኝ አስገብተው፣ እናታቸው ተከናንባ የተኛችበትን ብሉኮ ገፍፈው፣ "ይቻትልህ!" እንዳሉት አጅሬዎች አይደለሁም"
#የስንብት_ቀለማት








