Tilahun Tsige (@Menilikism) header
Tilahun Tsige (@Menilikism) profile picture

In this world, I found it irrational to be rational! I'm just a perspective of a perspective! 🤷

Dembia, Gonder
Joined April 2017
Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)Photo by Tilahun Tsige (@Menilikism)
ሀገር!
47
100
19
996
Tilahun Tsige retweeted
ስለ ዴቪድ ቤንጎሪዮን ምን ያህል ያውቃሉ? ዴቪድ ቤን ጎሪዮን በአይሁድ ህዝብ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ሚና የተጫውቱ አይሁዳዊያን በአባቶቻችን እርስት እንኖር ዘንድ ይደረግ ለነበረው ትግል እንዲሁም የአይሁድ ሉዓላዊት አገር ለመመስረት ይታለም የነበረውን ህልም ወደ እውነታ የቀየሩ ትልቅ መሪ ነበሩ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እስራኤል ነፃነቷን ከማግኘቷ ከረጅም ጊዜ በፊት ለዘማናዊቷ እስራኤል መሰረተ-ልማቶችን የዘረጉ መሪ ነበሩ። እ.ኤ.አ. ግንቦት 14 ቀን 1948 በቴል አቪቭ ከተማ የእስራኤልን የነፃነት አዋጅ በማንበብ አዲሷ እስራኤል መመስረቷን ለዓለም መንግሥታት ይፋ ያደረጉ በመቀጠልም የእስራኤል የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትርም ሆነው ያገለገሉ ናቸው። የቤን ጉሪዮን ቀን እየተከበረ ባለበት በዚህ ወቅት የእስራኤልን ነፃነት በማዎጅ እና ለዘመናዊት እስራኤል ላበረከቱት ጉልህ እስተዋጽዖ፣ ጀግንነትና ቁርጠኝነት የተሞላበት መንግስታዊ አመራር ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን።🇮🇱❤️
2
4
19
641
Searching Media Cloud for Ethiopia, Eritrea, Sudan and Somalia, we found the same 1,867 stories from 3 U.S. regional sites in all four, up to 92% of results. My new Inform Africa investigation on how narratives and flawed data obscure Horn crises: informafrica.net/2026/11/14/…
1
1
2
899
This picture is one of my favorites. I took it five years ago when I went to Gondar for the New Year. @Gfasil asked me to send him pictures of the village and its surroundings. I sent him many, including this lamb. He posted this one. Fasil was a little bit of everything. He loves random but beautiful things. Rest in peace, @Gfasil 🕊️
2
5
1
44
2,315
Why @Gfasil? why? ኧረ በጣም ይደብራል። ወይኔ ወንድሜ። 😭😭😢😢
4
27
981
እሺ አሁን ይሄንን ዜና እንዴት አምነን እንቀበለው? ምንስ ይባላል? እጅግ በጣም ነው የማዝነው። 😢😢😢
የምንወደው ወንድማችን ሰይፈ ሥላሴ (@Gfasil) ጥቅምት 22 ባደረበት ድንገተኛ ህመም ከዚህ ዓለም ድካም አርፏል💔 ሞቱን ከሰማሁባት ቅፅፈት ጀምሮ ለማመን ቢከብደኝም ወንድማችን ሳይነግረን፣ ደግመን ሳንጫወት ክፉ ሞት ነጠቀን🥺
1
3
32
1,865
In a fast changing region where conflicts, diplomatic rifts, political instability, and climate change coexist with hopes for peace, security, and development, #EastAfrica and the #GreatLakes face complex challenges and opportunities. In this episode, Horn Frequency sits down with @NgogaFred, a senior peace and security expert, to explore these regional dynamics. youtu.be/rhpdRVjN3yo?si=4jtw…
1
3
1
7
1,256
Tilahun Tsige retweeted
ደረጀ ደገፋው 1983 ዕዳ፣ በ1991 የልጅነት ህልሜ አልበምና በርካታ ስራዎችን ሰርቷል፣ ከፍቅር አዲስ፣ከማርታ ሃይሉ ጋርም ሰርቷል እንዲሁም ከ1991 አልበሙ መጠሪያ "የልጅነት ህልሜ" በሚለው ከልባችን የማይጠፋ ቅርስ የሆነ ሙዚቃ ሰርቷል። ...1
3
1
22
2,564
Tilahun Tsige retweeted
Today Israel celebrates Sigd, one of the most beautiful and ancient holidays of Ethiopian Jews, a day of renewal, unity, and longing for Jerusalem that predates modern Israel by centuries. 🇪🇹🇮🇱 A thread 🧵: Photo by Yonatan Sindel/Flash90
1
15
1
79
4,653
MOURNING & JUSTICE: THE 6TH ANNIVERSARY OF THE MAI KADRA GENOCIDE Six years ago today, the town of Mai Kadra became the site of one of the most horrific atrocities in modern African history. Over 1,600+ innocent Amhara daily laborers, mothers, and fathers were targeted, hunted, and systematically slaughtered solely because of their identity. We extend our profound gratitude to Canadian journalist and author Jeff Pearce @jeffpropulsion, whose fearless on-site investigation and field report in Mai Kadra documented the mass graves, preserved survivor testimonies, and challenged the false narratives surrounding this massacre. As we mark this somber 6th anniversary, we issue a stern political call to action: 1. Justice Cannot Be Traded: Political deals, opportunistic coalitions, and impunity for perpetrators will never erase the historical truth documented by human rights organizations, journalists, and survivors. 2. End Proxy Mercenarism: The criminal elements responsible for Mai Kadra must face international legal accountability, regardless of where they seek refuge or under whose proxy banners they operate. 3. Preserve Historical Truth: Mai Kadra remains an indelible reminder of systemic identity-based targeting. True peace can only be built on accountability, legal restitution, and the complete dismantling of genocidal structures. We honor the martyrs of Mai Kadra. Their blood demands justice, not silence. Reminder The Mai Kadra massacre was led by Colonel Yenane and General Fiseha Kidanu (Fiseha Manjus), or, as referred to by Zemene Kasse "Fish". Justice for Mai Kadra. Justice for all victims of identity-based violence. #AmharaGenocide #NeverForget #MaiKadra6thAnniversary #HumanRights #Ethiopia #JusticeNowForAmhara
1
16
1
12
965
ጠበቃው ዘውዱ ከማይካድራው እልቂት የተረፉ ሰዎች ካወሯቸው አሰቃቂ ታሪኮች መካከል፣ የጠበቃው ዘውዱ ታሪክ ልቤን በጥልቅ ነክቶታል። ምክንያቱም፣ በእልቂቱ የተገደሉ ብዙ ሰዎች ሞት ፊት ለፊታቸው በተደቀነበት በዚያ የመጨረሻ ቅጽበት ምን ያህል ፍርሃትና ሥቃይ እንዳሳለፉ እንዳስብ ያደርገኛል። አማራ በመሆንህ ብቻ ለጥቃት መዳረግ፣ በቆንጨራና በሳንጃ መወጋት፣ በፈላ ዘይትና ውሃ መቃጠል፣ በቤተሰብህ ፊት መሰቃየት፤ ይህን ሁሉ ማሰብ እጅግ ያማል። በእናት፣ በአባት ወይም በወንድም ፊት በሕፃን ልጅ ላይ የጾታ ጥቃት ሲፈጸም ማየት፣ በተጎጂዋም ሆነ በቤተሰቧ ላይ ጥልቅ የሥነ ልቦና ቁስል ይተዋል። የዚህ ወንጀል ኀፍረትና ውርደት የወንጀለኞቹ ነው። እንዲህ ያለው ግፍ የሰውን ክብርና ነፃነት የሚገፍፍ፣ እንደ ሰው እኩል የመታየት መብቱንም የሚነፍግ ነው። ለዚህ ነው የጠበቃው ዘውዱ ታሪክ የብዙዎችን ሰቆቃ የሚያንጸባርቅ መስተዋት ነው የምለው። ታሪኩም፣ ከተረፉት ሰዎች እንደተሰማው፣ እንዲህ ነው። ኅዳር አንድ ቀን 2013 ዓ.ም.፣ አማራዎችን እየፈለጉ የሚገድሉ፣ የሕወሓት «ሳምሪ» ቡድን አባላት እንደነበሩ የተገለጹ ነፍሰ ገዳዮች፣ በማይካድራ ወደሚገኘው የጠበቃው ቤት ገቡ። በዚያን ጊዜ ጠበቃው በቤቱ ጣሪያ ሥር ተደብቆ ነበር። ታጣቂዎቹ ቢፈልጉትም ሊያገኙት አልቻሉም። በመጨረሻም የ11 ዓመት ልጁን ይዘው፣ አባቱ ከተደበቀበት ካልወጣ ልጁን እንደሚገድሉ ዛቱ። ጠበቃው የልጁን ሕይወት ለማትረፍ ከተደበቀበት ወጣ። እነዚያ የቡድኑ አባላትም በዚያው፣ በሚስቱና በልጁ ፊት፣ በጭካኔ ገደሉት። ከዚህ ታሪክ ሁሉ ይበልጥ ልቤን የሚሰብረው፣ ያ የአባትና የልጅ የመጨረሻ ቅጽበት ነው። ምን እንደሚጠብቀው እያወቀ፣ ልጁን ለማዳን ከተደበቀበት የወጣ አባት፤ የአባቱን ፍቅርና መሥዋዕትነት እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ ያየ ሕፃን። ይህን ማሰብ ብቻ ልብን ይሰብራል። እነሆ፣ የግፍ እልቂት ስድስት ዓመታት ሞላው። ለዚያ ልጅ ፍትሕ ማለት ምን ማለት ነው? ፍትሕ በየዓመቱ ሻማ በማብራትና አባቱን በማስታወስ ብቻ አይረጋገጥም። ፍትሕ የሚረጋገጠው ወንጀሉን የፈጸሙት የህዋት ቡድን ሲሆኑ፣ እውነቱ ሳይደበቅ ሲገለጥ፣ የተጎጂዎችም ሥቃይ ለፖለቲካ ጥቅም መደራደሪያ መሆኑ ሲቀር ነው። ስለ ሟቾች ክብር እየተናገሩ፣ በእነሱ ላይ በተፈጸመው ግፍ የተሳትፈው የሕወሓት «ሳምሪ» ቡድን አባላትን ለፖለቲካ ጥቅም ሲባል ማቀፍ፣ ለእኔ ፈጽሞ ሊታረቅ የማይችል የሞራል ተቃርኖ ነው። የጠበቃው ልጅ፣ አባቱ እሱን ለማዳን የከፈለው መሥዋዕትነት ከንቱ እንዳልቀረ፣ የአባቱ ሕይወት ዋጋ እንደነበረው፣ ለፖለቲካ ስሌት ሲባልም በአባቱ ደም የማይደራደሩ ሰዎች አሁንም እንዳሉ እያወቀ እንዲያድግ እመኛለሁ።
1
22
3
41
1,374
The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church believers in the Arsi Zone of the Oromia region have been under persistent attack. Christians in this area have no protection from the government, making its security apparatus complicit in ongoing religiously motivated killings. ​These recurring attacks need immediate attention from the international community, as things are getting worse day by day. Media outlets, international human rights organizations, governments, and advocates should make this horrific situation one of their top priorities!
1
56
3
74
2,189
Today, we mark 31 years since the assassination of Prime Minister Yitzhak Rabin. We remember his unwavering commitment to Israel’s security, his dedication to the State of Israel, and his determination to pursue peace against all odds. His legacy reminds us of the importance of unity, democracy, and rejecting political violence. 🕯️ May his memory be a blessing. יהי זכרו ברוך
74
194
15
881
29,596
The United States is deeply concerned about recent reports of targeted killings of civilians in Arsi zone, Oromia region, Ethiopia. The United States condemns religious, ethnic, or political motivated violence. Such horrific attacks against any group must stop. As we seek to understand this tragedy, the United States urges against characterizations that could deepen division. The United States calls on the government of Ethiopia to investigate and to bring the perpetrators to justice.
257
948
85
1,793
113,799
Tilahun Tsige retweeted
At least 60 Christians have been killed in attacks in Ethiopia. More than 20 homes have been burned. The persecution of Christians cannot be ignored, and those responsible must be held accountable. We must stand with our brothers and sisters in Christ.
121
696
25
1,673
26,505
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የበለጠ ለጥቃት ተጋላጭ በምትሆንባቸው እንደ አርሲ ባሉ የሽብርተኞች እና አክራሪዎች መፈልፈያ አካባቢዎች የሚፈፀሙ ጥቃቶች እንዲሁ በቀላሉ ሊቆሙ የሚችሉ አይደሉም። መንግሥት ራሱ ባመነው እንደዚሁም እንደ አሜሪካ ያሉ መንግሥታት በተጨባጭ የሚያውቁት በአርሲ እና በባሌ ከኢትዮጵያ አልፎ እስከ ሶማሊያ እና የመን የተዘረጋ የሽብር ኔትዎርክ አለ። የአልሸባብ እና አይኤስ አይኤስ አባላት ከኢትዮጵያ ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳሻቸው ይወጣሉ፤ ከውጭ ወደ ኢትዮጵያም ይገባሉ። በመንግሥት የተያዙም ያልተያዙም አሉ። ተይዘው የተለቀቁም ይኖራሉ። አርሲ ተብሎ በሚጠራው የደም መሬት ክርስቲያኖች በግፍ ይገደላሉ። አንድ ሁለት ወራት ያልፋሉ። መልሰው ይገደላሉ። ወራት ያልፋሉ። ከእንደገና ይገደላሉ። ለማናውቀው ጊዜ ያክል ይህ አዙሪት ይቀጥላል። ምክንያቱም ጭፍጨፋውን ለማስቆም ኃላፊነት የተጣለበት መንግሥት መዋቅሩን በክርስቲያኖች ላይ ጥቃት ለሚያደርሱ አካላት ምቹ አድርጎታል። ራሱ መዋቅሩም ይሳተፍበታል። ለምን የሚለውን መደጋገም ስለሚሆን እንተወው። አድካሚ ነው። ዜጎች በሰላም ወጥተው እንዲገቡ የሚጠብቃቸው መንግሥት በሀገር ውስጥ እንደሌለ ሁሉም ያውቀዋል። በአርሲ እና መሰል ቦታዎች በክርስቲያኖች ላይ የሚፈፀመው ጥቃት ሊቆም የሚችለው ጉዳዩ ዓለምአቀፍ ትኩረት ሲያገኝ ነው። ልክ ለዓመታት የቀጠለው እና ኋላ አሜሪካን ጨምሮ የውጭውን ዓለም ትኩረት እንዳገኘው እንደ የናይጄሪያው "ቦርኖ" ግዛት ክርስቲያኖች ጥቃት። ለዚህ ደግሞ መልካም የሚባሉ አጋጣሚዎች አሉ። ከአፍሪካ እስከ መካከለኛው ምስራቅ ከአውሮፓ እስከ ሰሜን አሜሪካ ያሉ ትልልቅ የዓለም ሚዲያዎች የአርሲ ክርስቲያኖችን ግድያ ሽፋን እየሰጡት ይገኛሉ። በአርሲና አካባቢው የሚፈፀመው ጥቃት ከአንደኛው የዓለም ጫፍ እስከ ሌላኛው እየተሰማ ነው። ለዛውም ባልተለመደ ሁኔታ። ጉዳዩ ከዜና ሽፋን ባለፈ በተጨባጭ ተፅዕኖ የሚፈጥር እና ልዩ ትኩረት የሚያሻው እንዲሆን መስራት ያስፈልጋል። Globalized attention ማምጣት ያስፈልጋል። የዓለም ነባራዊ ሁኔታን ጨምሮ በርካታ አስቻይ መንገዶች አሉ። ይታሰብበት!
2
49
99
3,181
ጃዋር መሐመድ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አሁን በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ያለውን ግጭት ካዋለዱት ሂደቶች ቢያንስ በአንዱ ተሳታፊ ነበር። ጃዋር አብሮ ከተሳተፈባቸው እና አሁን ያለውን ውጥረት ካዋለዱት ሂደቶች መካከል አንደኛው ከጥቂት ወራት በፊት "የማኅበራዊ ሚዲያ ትዕይንተ ሕዝብ" የተባለው ስብስብ ያካሄደው ስብሰባ አንዱ ነው። ይህ ስብስብ ለስሙ "በኢትዮጵያ የተቃውሞ ጎራ ያሉ ኃይሎችን ያቀፈ" ቢባልም ፕሮጀክቱ ግን የሻዕቢያ እና የህወሓት እንደነበር የቅርብ ጊዜ ትዝታ ነው። በስብስቡ ውስጥ ኢሳያስ አፈወርቂን ጨምሮ ከሻዕቢያ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያላቸው፣ እንደዚሁም ከሀገር ውስጥ እስከ ውጭ ሀገር የሚኖሩ በድብቅ እና በይፋ ወደ አስመራ የሚመላለሱ ሰዎች ሲዘውሩት የነበረ ስብስብ ነው። ጃዋር እነማን ከጀርባ እንዳሉ እንደዚሁም የዚህ እንቅስቃሴ Ultimate ግቡ (በሻዕቢያ እገዛ መንግሥትን መገልበጥ) እንደሆነ እያወቀ ነበር የዚህ እንቅስቃሴ አካል የሆነው። ፅምዶ (ትብብር ለኅልውና) የተባለው የሻዕቢያ የእጅ ስራም የዚሁ እንቅስቃሴ ተቀጥላ ነው። ጃዋር በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት በኩል ፅምዶን የማዋለወድ ሂደት አማካሪም ነበር። እንደ አሁኑ ይፋዊ በሆነ መልኩ ባይሆንም የኤርትራ ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠው ከወታደራዊ ድጋፍ እስከቀጥተኛ የውጊያ ተሳትፎ ማድረግ ከጀመሩ ቆይተዋል። የኢትዮጵያ መንግሥትም ጉዳዩን ወደተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እስከመውሰድ ደርሶ ነበር። ጃዋርም ይሄንኑ ጠንቅቆ ያውቃል። እያወቀ ግን የሂደቱ ተሳታፊ ነበር። ጃዋር OMNን ይመራ በነበረበት ጊዜ ሚዲያው አስመራ ድረስ ተጉዞ ኢሳያስ አፈወርቂን ቃለምልልስ ያደረገበትን ጨምሮ የድሮ ታሪኩን እንተወውና፣ በ2018 ዓ.ም ውስጥ ብቻ ጃዋር መሐመድ ራሱ "ለሀገረ መንግሥቱ ስጋት ናቸው" በሚላቸው እንቅስቃሴዎች ቀጥተኛ ተሳታፊ ነበር። እነዚህ እንቅስቃሴዎች ናቸው እንግዲህ ሄደው ሄደው ዛሬ ያለንበትን ሁኔታ ያዋለዱት። ታዲያ በምን ሞራሉ ነው እርሱ ሌሎችን "ከፀረ ኢትዮጵያውያን ጋር ተጣመሩ" ብሎ ለመክሰስ የቻለው? የዚሁ አካል አልነበርክምዴ ኦቦ @Jawar_Mohammed? ተው እንጅ። ትንሽ አረጋጋው እንጅ! 😆 ከዚሁ ጋር በተያያዘ፣ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ሀገሩን ከውጭ ኃይሎች ወረራ የመጠበቅ፣ የሀገሩ ብሔራዊ ጥቅሞችም ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ ለማድረግ የዜግነት ግዴታውን መወጣት አለበት ብዬ አምናለሁ። ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚል ሰውም (Irrespective of what government is leading the country) በሁለት ነገሮች የማይዛነፍ አቋም ሊኖረው ይገባል የሚል ፅኑ ዕምነት አለኝ። በዓባይ ወንዝ ጉዳይ እና በኢትዮጵያ ታሪካዊ የባሕር በር ጥያቄ ዙሪያ። እነዚህ ሁለት ጉዳዮች በኢትዮጵያ ታሪክ የውጭ ግንኙነት ማጠንጠኛ ሆነው ያገለገሉ ናቸው። ይቀጥላሉም። ጃዋር ከሰሞኑ የሀገረ-መንግሥቱ ጠበቃ ሆኖ ከመምጣቱ ጋር ችግር የለብኝም። ከመርህ አንፃር ገዥ የሆኑ ሃሳቦችንም ሲያነሳ ተመልክቻለሁ። በዚህ ተቃውሞ የለኝም። ነገር ግን በደምና አጥነት የተፃፈውን የኢትዮጵያን ታሪክ በማንቋሸሽ የፖለቲካ ስብዕናውን ሲገነባ የኖረ ሰው ንስሐ ሊገባ ይገባል እንጅ ሌሎችን የመክሰስ እንጥፍጣፊ ሞራል የለውም።
10
7
1
36
8,093
Making sense of what's unfolding in the North! ...... Though it is still unclear what the real purpose of the war is, the entire northern part of Ethiopia is once again unraveling due to war. 👉Tigray! .... The TPLF's breakaway faction, consisting of Tigray Peace Force (TPF) and Simret Party led by Getachew Reda and Tsadikan G/Tinsay is emerging in and taking control of Tigray, unless the TPLF regains momentum very soon. This group is perceived as loyal to Abiy Ahmed, having been backed by the federal government both militarily and politically. A new political group with a military wing is likely to persist in Tigray even if the TPLF-led ruling elite demises. Getachew heads the political and diplomatic wing, while Tsadikan leads the military wing. TPLF-led Tigray nationalism has entered a slow-decline dynamic. Time will tell how this development will shape the Tigray-Amhara relationship, including long-standing territorial disputes. 👉​Eritrea! ...... Eritrea's role in the ongoing conflict stems from two main factors: its spoiler role in the Pretoria Peace Agreement process and Abiy Ahmed’s quest for direct sea access, demonstrated by the signing of the failed Memorandum of Understanding with Somaliland and followed by Ethiopia's historical claim of Assab. Moreover, despite its continuous denials, the Ethiopian government has accused Eritrea of covertly supporting armed groups in Ethiopia, reviving a historical pattern of backing Ethiopian opposition groups dating back to the "no-peace, no-war" period. Ethiopia's accusations materialized when Eritrean troops reportedly crossed the Ethiopian border in support of the TPLF, though the ENDF successfully pushed them back. Despite this, a full-scale war remains unlikely unless Ethiopia's Red Sea ambitions accelerate the situation in real time, though other driving factors could still apply. This raises a critical question: Would marching on Assab or Asmara be the right way to advance Ethiopia's Red Sea ambitions if a full-scale war becomes inevitable? And what would be the fate of the regime in Asmara? A web of complex consequences would inevitably follow. 👉Implications for the Horn of Africa! ..... The fragile Horn of Africa region is already enduring a prolonged proxy war in Sudan, one of the deadliest globally in recent times. If tensions between Ethiopia and Eritrea escalate into a full-scale war, the entire region risks becoming a battleground for competing regional powers, leaving states of the Horn of Africa entirely stripped of control.
1
1
1
6
1,503
ህወሓት የፕሪቶሪያውን፣ ዐቢይ አህመድ የጅዳውን ስምምነት ቀደዱ! …………… ከአሥር ወራት በፊት በኅዳር 2018 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶክተር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ "ያልተፃፈው የኢሳያስ አፈወርቂ አስተምህሮ" እና "የናቅፋ በሽታ" ሲሉ የሰየሟቸውን ሁለት ምክንያቶች ጨምሮ በጥቅሉ አምስት መሰረታዊ ችግሮች የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነት "ወደለዬለት ውጥረት" እንዲሸጋገር አድርገዋል ሲሉ መደመጣቸው ይታወሳል። የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ይሄንን ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሲሆን፣ ጉዳዩ የዓለም አቀፍ ትኩረትን የሳበ እና በርካቶች አስተያየታቸውን የሰጡበት አጀንዳ ነበር። ጌዲዮን የሁለቱን ሀገራት ወቅታዊ ግንኙነት ቃል በቃል "Chronic Tension" በማለት ነበር የገለፁት። ከሰባት ወራት በፊት ማለትም ባሳለፍነው የካቲት ወር 2018 ዓ.ም International Crisis Group ሁለት ተከታታይ ጥናታዊ ፅሁፎችን አውጥቶ ነበር። በቅድሚያ "Seven Peace and Security Priorities for Africa in 2026" የሚል ፅሁፍ ያወጣ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ጉዳይ ከሰባቱ የአፍሪካ አሳሳቢ የፀጥታ ጉዳዮች አንደኛው እንደሆነ የሚያትት ነበር። ከሳምንት በኋላ ሁለተኛው እና የሁለቱን ሀገራት እንደዚሁም የፌደራል መንግሥቱን እና የህወሓትን ውጥረት አስመልክቶ "Ethiopia, Eritrea and Tigray: A Powder Keg in the Horn of Africa" የሚል ረዥም ፅሁፍ አወጣ። ተቋሙ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት “በአፍሪካ ቀንድ በማንኛውም ቅፅበት ሊፈነዳ የሚችል የባሩድ በርሜል” ሲል ነበር የገለፀው። የእነ ደብረፅዮንን ህወሓት ጨምሮ "ለኢትዮጵያ ታጣቂ ቡድኖች ድጋፍ ታደርጋለች" የሚል ክስ በኤርትራ ላይ መቅረቡ፣ በምላሹ የኢትዮጵያ መንግሥት ለኤርትራ የተቃዋሚ ቡድኖች እና ከህወሓት ለተገነጠለው ሌላኛው ታጣቂ ቡድን ድጋፍ ያደርጋል መባሉ፣ ከሱማሌላንድ በኋላ ወደ ቀይ ባሕር የዞረው የኢትዮጵያ የባሕር በር ፍላጎት፣ የአፍሪካ ቀንድ ቀጠናዊ ውጥረት እና የኃያላኑ ጅኦ-ፖለቲካዊ ፍላጎቶች እንደ ተጨማሪ ገፊ ምክንያት ሆነው ሲመጡ፣ የሁለቱ ሀገራት ጉዳይ በርግጥም በአፍሪካ ቀንድ በማንኛውም ሰዓት ሊፈነዳ የሚችል ፈንጂ ተብሎ የሚገለፅ ነው። የኢትዮጵያ መንግሥት በአስመራ የሚገኘውን ኤምባሲ ለመዝጋት መወሰኑ የዚሁ ማሳያ ተደርጎ የሚወሰድ ነው። ከአንድ ሳምንት በፊት ህወሓት የፕሪቶሪያውን ስምምነት ቀድጃለሁ፣ ጦርነትም አውጃለሁ ብላለች። ዐቢይ አህመድ ደግሞ በመስከረም 2011 ዓ.ም ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ግንኙነታቸውን መልሰው ያደሱበትን የጅዳውን ስምምነት በዛሬው ዕለት በይፋ ቀድደውታል። እስራኤል፣ የተባበሩት አረብ ኢመሬቶች፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብፅ፣ ኳታር፣ ኢራን እና መሰል ሀገራት "Physical Border" የሌላቸው የአፍሪካ ቀንድ ሀገራት እስኪመስሉ ድረስ በቀጠናው ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያላቸው ሀገራት ሆነዋል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ውጥረት ወደ ጦርነት የሚያመራ ከሆነ እነዚህ ሀገራት ጎራ ለይተው ጎራዴ ለመምዘዝም ዝግጁ ናቸው።
1
3
8
3,529
Mesqel! The Ethiopian Orthodox Tewahdo Church commemorating the discovery of the True Cross!
1
3
69
2,184
፩ 52 ዓመታት! ደርግ መጣ። ለግማሽ ክፍለ ዘመን የቀጠለ "ደርገኝነትን" እና "ደርጋዊነትን" የኢትዮጵያ ፖለቲካ ባህል አድርጎ ሄደ። ደርግ! ……… በአዲስ ዓመት ማግስት በመስከርም ወር ሁለተኛ ቀን በ1967 ዓ.ም ደርግ የተባለ የአኩራፊ ወታደሮች ስብስብ ጃንሆይን በቆራጣ ወረቀት መነባንብ "ከስልጣን ወርደዋል" አላቸው። ጊዜው መድረሱን የተረዱት ግርማዊነታቸውም የሚከተለውን አጭር ንግግር ለታሪክ ይቀመጥ ዘንድ ተናገሩ። "የእኛ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል፤ የእናንተ ታሪክ ከዚህ ይጀምራል። ነገር ግን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ማስከበር ካቃታችሁ፣ ያን ጊዜ የእናንተ ታሪክ ይሞትና የእኛ ታሪክ በድጋሚ ይጀምራል!” በርግጥ ቀ.ኃ.ሥ በዚህ ዕለት ይሄንን ይበሉ እንጅ ዛሬም ድረስ ጎልቶ የሚታየው የእሳቸው ታሪክ መልሶ የጀመረው፣ በስርነቀል ለውጥ እና አብዮት ስም ኢትዮጵያን አዘቅት ውስጥ ጥሎ ያለፈው የደርግ ታሪክ ያከተመውም የዚያኑ ቀን ነበር። ከመስከረም 2 1967 ዓ.ም ወዲህ በኢትዮጵያ ምድር የተከሰቱ ነገሮች በሙሉ የሚነግሩን እውነት ይህንን ነው። የቀዝቃዛውን ጦርነት መጠናቀቅ ተከትሎ ፍራንሲስ ፉኩያማ በፈረንጆቹ 1992 ዓ.ም "The End of History and the Last Man" በሚል ርዕሰ ባሳተመው መፅሀፉ ላይ፣ ዓለም ላይ የSocialism ዕሳቤ "Rigid" በሆነ መንገድ ከተተገበሩባቸው ሀገራት መካከል አንዷ ኢትዮጵያ መሆኗን ይገልፃል። ደርጋዊነት እና ደርገኝነት! ……… ከጃንሆይ ስንብት በኋላ የኢትዮጵያን ክብር አስጠብቀው ያቆዩ ታላላቅ ሰዎች ጊዜ በሰጣቸው ተራ ወታደሮች "ይገደሉ ይረሸኑ" እየተባሉ እጅ እየተወጣባቸው በመንጋ ፍርድ በግፍ የተጨፈጨፉት ወዲያውኑ ነበር። ይህ የታሪክ አጋጣሚ ዛሬም ድርስ አዙሪት ሆኖ የሚያንደፋድፈን ያኔ በተፈፀመው ግፍ ነው ብሎ በድፍረት መናገር ይቻላል። በዚህ ዘመን ነበር ሀገር ያቀኑ፣ በትምህርት፣ በእውቀት፣ እና በአብርሆት ከኢትዮጵያ አልፎ ለአፍሪካ ኩራት መሆን የቻሉ መሪዎች ገለል ተደርገው የፍትሕን እና ፍርድን ዋጋ በእጃቸው በያዙት ጠብመንጃ ብቻ በሚመዝኑ መለዮ ለባሾች መዳፍ ስር ሀገር የወደቀችው። ከዚህ ጊዜ በኋላ "አሳቢነት" በኢትዮጵያ ተነውሯል። ስልጣን የተቆናጠጠውም፣ ለስልጣን የሚታገለውም የፖለቲካ ልዩነትን የሚያስተናግደው በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት ሳይሆን በጠብመንጃ ወልዋይነት ነው። ኃይል ያለው የመሰለው ሁሉ "በሀሳቡ ከእኛ ወገን ያልሆነ ይገደል" ብሎ "ስቀለው ስቀለው" በሚል የመንጋ ጩኸት ታጅቦ ኢ-ፍትሐዊነትን ፍትሃዊ ሲያደርግ ኖሯል። አማራጭ ሃሳብ በባንዳነት ያስፈርጃል። "ይህ መንገድ ያጠፋናል ይሄኛውን እንሞክረው" ማለት ከክህደት ይቆጠራል። ያስነጥላል። ያስገድዳል። በቀልም አዙሪት ሆኖ ዛሬ ላይ ደርሰናል። ጃንሆይን ከስልጣን ካወረደው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ትይዩ "አማራ ጠልነት" በርዕዮተ-ዓለማዊ መንገድ በኢትዮጵያ ይቀነቀን ነበር። ደርግ ለአማራ ጠልነት ዕሳቤ አረንጓዴ መብራት አብርቶ፣ ራሱን እና የራሱን ሰዎች "በደርገኝነት" መንፈስ እየተመራ "በደርጋዊነት" ጭካኔ እየበላ ስልጣኑን ለአክራሪ ብሔርተኛው ኃይል አስረክቦ ዜጎች በጅምላ ተገድለው በጅምላ የሚቀበሩባት ሀገር እውን ሆናለች። ልክ እንደ 60ዎቹ የቀ.ኃ.ሥ ባለሥልጣናት። የደርጋዊነት ጭካኔ እና የደርገኝነት መንፈስ፣ ዛሬ ላይ ሳይቀር ለፍትሕ እና ነፃነት እንታገላለን የሚለውን ኃይል ተጣብቶት ለአንድ ዓላማ፣ ለአንድ ሕዝብ ዕጣፋንታ ለትግል የወጡ ወንድሞቹን የሃሳብ ልዩነት ስላንፀባረቁ ብቻ "እንደጀመርናቸው እንጨርሳቸዋለን" አስብሏል። ክፉ መንፈስ ነውና። ደርግ፣ ደርጋዊነት፣ እና ደርገኝነት ለሀገርና ሕዝብ የደከሙ ታላላቅ ሰዎችን በልቷል። አማራን ለከፉ ደርገኞች አሳልፎ ከሰጠ ግማሽ ክፍለ ዘመን ተሻግሯል። "ኢትዮጵያ ትቅደም" እያለ ኢትዮጵያን ያስቀደሙትን እና ሀገር ያቀኑትን "ክሬም ጭንቅላቶችን" ረሽኗል። "ቀይ ባሕርችን አይደፈርም" እያለ የባሕር በር ድንበር ያስከበሩትን፣ የኢትዮጵያን ታሪካዊ የውሃ ጠረፍ ያስጠበቁ እንቁዎችን ቀርጥፎ በልቷል። ኢትዮጵያን በአካሏ እንድትከረከም አድርጓታል።
4
6
18
1,944
፪ ጃንሆይ! …… "የእኛ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል፤ የእናንተ ታሪክ ከዚህ ይጀምራል። ነገር ግን የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ማስከበር ካቃታችሁ፣ ያን ጊዜ የእናንተ ታሪክ ይሞት እና የእኛ ታሪክ በድጋሚ ይጀምራል!” ……… ጃንሆይ ከወረዱ በኋላ አንድ ዓመት እንኳን ሳይቆዩ ነበር የተገደሉት። ታሪካቸው ግን ከስልጣን በወረዱበት በመስከረም 2 1967 ዓ.ም ቀን ነበር መልሶ የጀመረው። ከዚህ በኋላ በዓለም አደባባይ የእሳቸውን ያህል እውቅና እና ክብር ያገኘ መሪ በኢትዮጵያ ምድር አልተፈጠረም። የግርማዊነታቸው ታሪክ እንደ ቃላቸው መልሶ የጀመረው ከስልጣን በወረዱበት ቀን መስከረም 2 1967 ዓ.ም ስለመሆኑ ሀገራችን ከዛ ጊዜ ወዲህ ያለፈችባቸው ፈተናዎች ምስክር ናቸው። ትምህርት ብትል የእሳቸውን ስም ሳትጠራ ማውራት አትችልም። የባሕር በር ብትል የቀ.ኃ.ሥ ስም ከፊት አለ። ዲፕሎማሲን ብትጠራ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት Climax በእሳቸው ዘመን ነው። ዓባይ ግድብ ብትል የልማት ውጥኑም እዚሁ ነው። ዘመናዊነት ብትል የዘመናዊት ኢትዮጵያ ችቦ ለኳሽ ናቸው። ከ52 ዓመታት በኋላ ዛሬም ድረስ ሌጋሲያቸው ቀጥሏል! ይቀጥላልም።
3
245