የድሮን ምርምርና ልማትን ለማጠናከር የሚያግዝ ስምምነት ተፈረመ
የስካይዊን ኤሮናቲክስ ኢንዱስትሪና የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስ እና ጂኦስፓሻል ኢንስቲትዩት የድሮን ምርምርና ልማትን ለማጠናከር የሚያግዝ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡
በሁለቱ ተቋማት መካከል የተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ የኢትዮጵያን የኤሮናቲክስ ቴክኖሎጂ አቅም ለማሳደግ፣ የድሮን ምርምርና ልማትን ለማጠናከር እንዲሁም የአየር ላይ ቅየሳ አገልግሎትን ለማስፋፋት ያለመ ነው፡፡
ዓለም ከስሟ ባሻገር እንቁ ታሪኳን በሙሉ ጠንቅቆ ያላወቀላት ኢትዮጵያ፤ ዛሬ ታሪኳን በራሷ ድምፅና በራሷ ብዕር ለዓለም ታስተዋውቃለች። ይፋዊው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ድረ-ገጽ ይፋ ሆኗል!
ቡናን ከጫካዎቿ አፍልቃ ለዓለም ስጦታ ያበረከተች፣ የቡና ትውልድ ሀገር ኢትዮጵያ። የሰው ዘር የመጀመሪያ እርምጃውን የጀመረባትና አየሯን እስትንፋስ አድርጎ የተነፈሰባት ኢትዮጵያ። በአረንጓዴ ዐሻራ፣ በሕዝቦቿ እጆች ዳግም እየለመለመች ያለች ምድር፤ ኢትዮጵያ። ወንዞቿን፣ ነፋሷንና ፀሐይዋን ወደ ኃይል ቀይራ ከራሷም አልፋ ለጎረቤቶቿ ብርሃን የሆነች ኢትዮጵያ። ከተሞቿ በአዲስ ውበት እያበቡ በልባቸውም የአፍሪካን አዲሷን አበባ ታቅፈው የያዙ ኢትዮጵያ። አፍሪካውያን የጥቁር ሕዝቦችን ዘመን ተሻጋሪ ኩራትና ወኔ በፓን-አፍሪካዊ አንድነት ድምፅ ለመግለጽ የሚተሙባት ኢትዮጵያ። ጥንታዊ ሥልጣኔዋን ዛሬም በድንጋዮቿ፣ በፊደሎቿ፣ በዜማዎቿና በፕሮጀክቶቿ ሕያው አድርጋ የምታኖር ኢትዮጵያ። ሯጮቿም የድል መንፈሷን ከትውልድ ትውልድ እያስተላለፉ፣ በዓለም የድል መድረኮች የምታበራ ኢትዮጵያ!
ወደ ኮፕ32 በሚደረግ ታሪካዊ ጉዞ ይህ ድረ-ገጽ ከታሪካችን እስከ ዛሬ እርምጃችን፣ ከሥልጣኔያችን እስከ የወደፊት ርዕያችን ድረስ ያለውን የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት፣ ሀብትና ተስፋ ለዓለም የምናቀርብበት መድረክ ነው። ምድረ ቀደምትነቷን ይወቁ፤ የኢትዮጵያን ታሪክ ይመስክሩ!
🔗 ማስፈንጠርያ: ethiopia.gov.et/
ምድረ ቀደምት፤ ኢትዮጵያ 🇪🇹
#ኢትዮጵያ #LandOfOrigins #COP32Ethiopia
#PMOEthiopia
#የትግራይ_መረጃ!...
ሦሥት የህወኃት_ወያኔ የስለላ ማእከል አዛዦች በጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ተማረኩ። የአሸባሪው የህወኃት_ወያኔ ቡድን የስለለላ ማዕከል ኃላፊዎች በሳምሬ መስመር የጭላ የተባለ ቦታ ላይ ተማርከዋል።
በዚህም፦
➥ ብርጋዴር ጀነራል ኣባዲ ፊላንሳ፣
➥ ኮሎኔል ደጀን ግርማይ መስፍን፤
➥ ኮሎኔል ልኡል ኣይናለም፣
➥ መብራህቱ ገ/ሄር (ሹፌር) የተባሉት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለዋል ።
Ethiopia has taken delivery of 12 Russian-made Su-35 fighter jets and will later receive four S-400 air defence systems from Moscow as part of a drive to bolster its military capabilities, Ethiopian Prime Minister Abiy Ahmed says.
trtafrika.com/english/articl…
መረጃ
የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ በይፋ ትግራይ ክልል መቐለን ጨምሮ በሁሉም የትግራይ ዞን ስራውን ጀመረ።
አቶ ብርሃነ ገብርፃድቅ የትግራይ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት ሆነው እንዲያገለግሉ ተመደቡ።
እንኳን ደስ አለን አላችሁ የትግራይ ህዝብ🙏
ክብር ለጀግኖች ENDF & TPF 🙏🇪🇹
#ድል_ለእናት_ሀገራችን_ኢትዮጵያ 💪🇪🇹✊
❝...ከኢትዮጵያ፣ ከተባበሩት አርብ ኢምሬትስና የመጀመሪያውን እውቅና ከሰጠናት ሶማሊላንድ ጋር ጥብቅ ግንኙነት አለን። ኢትዮጵያ በቀጠናው ወሳኝ ሀገር ስትሆን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እጅግ ጠንካራ መሪ ነው። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) እስራኤልን በጎበኘበት ወቅት ደጋፊዬ መሆኑንና አብሮኝ ለመስራት ፍላጎት እንዳለው ገልጾልኛል...❞
- ቤንጃሚን ኔታንያሁ፣ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር
🇪🇹🤝🇮🇱
በሽሬ ከተማ 543 የጦርነት መገናኛ ሬዲዮዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ታውቋል።
በሕዝብ ጥቆማ እና በTPFና ENDF ሠራዊቶች ትብብር በሽሬ ከተማ የተደረገ ፍተሻ፤ ለጦርነት ዓላማ ሲውሉ የነበሩ 543 የተለያዩ የመገናኛ ሬዲዮዎች (እንደ 1187፣ Motorola፣ Harris እና ICOM ያሉ) እንዲሁም በርካታ መለዋወጫዎችና ቻርጀሮች በቁጥጥር ሥር ውለዋል ነው የተባለው።
አሁን DW Amharic እንዳረጋገጠው «ሌላ የጦር ጀነራል በከበባ ውስጥ ገብተዋል»
በትግራይ የተለያዩ አካባቢዎች የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የትግራይ የሰላም ኃይል በጋራ «የመቃረም» ያሉት ዘመቻ እንደቀጠለ ነው። በዛሬው ዕለት በክልሉ የማዕከላዊ ዞን የሚገኙ ከማይቅነጣል እስከ ወርቅአምባ ያሉ መንደሮች ነጻ መውጣታቸውን ታውቋል።
የኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄ፡- ከዲፕሎማሲያዊ ጥረት እስከ ባሕር ኃይል ግንባታ
*********************
ኢትዮጵያ የባሕር በር ጥያቄዋን እውን ለማድረግ የዲፕሎማሲ ጥረቷን እያጠናከረች የባሕር ኃይሏን መልሳ በማቋቋም የቀጣናውን ሰላምና ደኅንነት የማስጠበቅ አቅሟን ለማሳደግ እየሠራች ትገኛለች።
የባሕር በር ጉዳይ ከኢኮኖሚያዊ ጥቅም ባሻገር ከብሔራዊ ጥቅም እና ከሀገራዊ ሕልውና ጋር የተያያዘ ጉዳይ መሆኑን የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል አመራሮች ይገልጻሉ።
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ ካፒቴን ዝናቡ ዘንጌ ከኢቢሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ፣ ባሕር በርን ማንሳትና የባሕር ኃይልን ማቋቋም ቀደም ሲል ወደ ግጭት እንደሚያመራ ይታሰብ እንደነበረ አስታውሰው፣ አሁን ላይ ይህ አመለካከት መቀየሩን ገልጸዋል።
የባሕር በር ጥያቄ ብሔራዊ ጥቅምና የሕልውና ጉዳይ መሆኑ በይፋ መነሳቱን ጠቅሰው፣ የዲፕሎማሲ ሥራውም ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑን አስረድተዋል።
በቅርቡ የባሕር በር ለማግኘት የሚደረገው ጥረት እውን እንደሚሆን የሚያመለክቱ ሁኔታዎች እንዳሉም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ባሕር ኃይል ዋና አዛዥ ቫይስ አድሚራል ክንዱ ገዙ በበኩላቸው፣ ኢትዮጵያ በፖለቲካዊ ሂደቶች ምክንያት ያጣችውን ወደብ መልሳ የማግኘት ጥያቄ እያቀረበች መሆኗን ዓለም እየተረዳ መምጣቱን ገልጸዋል።
የባሕር በር ጥያቄውን እውን ማድረግ የትውልድ ኃላፊነት መሆኑን ጠቅሰው፣ ለዚህም የባሕር ኃይሉ የሰው ኃይልና የሙያ አቅም በማጠናከር ላይ መሆኑን አመልክተዋል።
ዋና አዛዡ እንደገለጹት፣ የሀገራችን ጥቅም በአሰብ ወደብ ብቻ የተገደበ አይደለም፤ በቀይ ባሕር፣ በሕንድ ውቅያኖስ እና ከዚያም ባሻገር ባሉ ዓለም አቀፍ የውሃ አካላት ላይ ሀገራችን የንግድና የደኅንነት ጥቅሞች አሏት፤ እነዚህን ጥቅሞች በሰላማዊ መንገድ ለማስከበር የሚደረገው ዝግጅት እየተጠናከረ ነው።
ኢትዮጵያ አውሮፓ ሕብረትን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ጋር በምታደርገው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት፣ የባሕር በር ጥያቄዋንና ታሪካዊ ዳራውን የማስረዳት ሥራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
የባሕር በር ማግኘት ጥያቄ ከባሕር ኃይል ግንባታ ጋር ተያይዞ የንግድ መርከቦችን እና የባሕር ላይ የኢኮኖሚ ጥቅሞችን የመጠበቅ ጉዳይንም ያካትታል ያሉት ዋና አዛዡ፣ ኢትዮጵያ በንግድ መርከቦች ላይ ያላት ተሳትፎ የባሕር ኃይል አቅሟን ማሳደግና በውሃ አካላት ላይ ያላትን ጥቅም ማስጠበቅ እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል።
የባሕር ኃይሉ ዕድገት ከሀገራችን አጠቃላይ የመከላከያ አቅም አንዱ አካል መሆኑን ጠቅሰው፣ ኢትዮጵያ በቀጣናው ያላት አቅም የባሕር ኃይልን ብቻ ሳይሆን የሌሎች የደኅንነት ዘርፎችንም እንደሚያካትት አስረድተዋል።
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድና በምስራቅ አፍሪካ የሰላም ማስከበር ሥራዎች የረጅም ጊዜ ልምድ ያላት ሀገር ናት። በሀገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ የሰላም ማስከበር ተልዕኮዎች ያላት ተሳትፎ፣ በቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ላይ የሚኖራትን አስተዋጽኦ ያሳያል። የባሕር ኃይሉ መጠናከርም ከዚህ አጠቃላይ የደኅንነት አቅም ግንባታ ጋር የተያያዘ ነው።
የባሕር በር ጥያቄ፣ የባሕር ኃይል ግንባታ እና ቀጣናዊ የሰላም ማስከበር አቅም የኢትዮጵያን የኢኮኖሚ፣ የደኅንነትና የዲፕሎማሲ ጥቅሞች ከማስጠበቅ ጋር የተያያዙ ጉዳዮች ናቸው።
የሀገራችንን ብሔራዊ ጥቅም በሰላማዊና በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማስከበር የሚደረገው ጥረት ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚቀጥል ኃላፊነት መሆኑንም አመራሮቹ አጽንኦት ሰጥተዋል።
#Ethiopia #EthiopianNavy #RedSea #NationalInterest #Diplomacy #RegionalSecurity
የኣርሚ 43 ኣዛዥ ሙርከኛ ሓጎስ ሓውዜን ይባልል
ትውልድን አስበልቶ አጀቢዎች ረግፈው ተማረከ እጅ ወደ ላይ አደረገ!
#ድል_ለእናት_ሀገራችን_ኢትዮጵያ 💪🇪🇹👊
የባሕር ዳር ሕዝብ ለሀገር መከላከያ ሠራዊቱ የቆመበት ታላቅ ቀን!
የሀገርን ሉዓላዊነትና ሰላም ለማስጠበቅ ሌት ተቀን ለሚተጉ ጀግኖች ሰራዊቶቻችን አጋርነታችንን ለማሳየት ዛሬ በባሕር ዳር ከተማ ደማቅ ሕዝባዊ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
ክብር ለሰራዊታችን! 🇪🇹
"...አንድ ትውልድ ለመስዋዕትነት መዘጋጀት አለበት። ሃምሳም ሆነ ስልሳ አመት ይፍጅ ፣ አንድ ትውልድ መስዋዕት ለመሆን መዘጋጀት ይገባዋል..."
ሙርኮኛው ጆን መዲድ




























